የተለያዩ እቃዎች ዉስን ጨረታ ይመለከታል

መቐለ ዩንቨርስቲ

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የሕብረተሰብ ሳይንስ ቋንቋዎች ኮሌጅ ለትያትር አርትና የሙዚቃ ትክፍል አገልግሎት የሚዉል የተለያዩ እቃ በዉስን ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱት ዝርዝር የመወዳደሪያ መመሪያዎች መሰረት እንድትወዳደሩ እናስታዉቃለን

1 ተወዳዳሪዎች በዘረፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ

2 ተወዳዳሪዎች የሚቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ VAT ጨምረዉ ዋጋዉ መሙላት አለባቸዉ

3 ተወዳዳሪዎች የተጠቀሰዉ እቃ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ

4 ተወዳዳሪዎች በሚቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸዉን : ፈርማቸዉና ሙሉ አድራሻቸዉ መግለፅ አለባቸዉ ::በተጨማሪም በፖስታዉ ላይ ሙሉ አድራሻ የጨረታ መለያ ቁጥር በመፃፍ ወደ ኮለጁ ገቢ ማድረግ አለባቸዉ

5 ተወዳዳሪዎች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ: የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ: የምዝገባ ምስክር ወረቀት የ VAT ምስክር ወረቀት ኮፒ ከመወዳደሪያ ዋጋቸዉ በሁለት በፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት አሽገዉ ማቅረብ አለባቸዉ

6 ተወዳደሪዎች ዉስን ጨረታዉ ከተከፈተ በኃላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሓሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም

7 ጨረታዉ ለመዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ዉጭ እነደሚሆኑና ለወደፈት ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል

8 ተወዳደሪዎች የዉስን ጨረታዉ ማስከበሪያ ብር 2000.00 በመቀሌ ዩንቨርስቲ የሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ስም C.P.O ማስያዝ አለባቸዉ

9 አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉ እቃ በራሱ ወጪና ትራንስፖርት እቃዎች ወደ መቀለ ዩነቨርስቲ ማድረስ አለበት

10 ተጫራቾች በመቀሌ ዩንቨርስቲ የሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ በተዘጋጀዉ ቃለ ማሃላ ቅፅ በድጅታቸዉ ስም ፈርመዉ የድጅታቸዉ ማህተም አድርገዉ ማቅረብ ይኖርባችዋል

11 ኮሌጁ የሚገዛዉን እቃ ብዛት እንደ ኣስፈላጊነቱ እስክ 20% /ሃያ በመቶ/ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል

12 ዉስን ጨረታዉ በሁለት በሰም በታሽገ ኢንቨሎፕ የሚቀርብ ሲሆን ዋናዉና ቅጂ ሰነድ በድርጅቱ ስልጣን ባለዉ አካል ፊርማና ማህተም ሊኖረዉ ይገባል የንግድ ፍቃድ ኮፒ: የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት (TIN) ኮፒ :የኣቅረቢ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ  :VAT ምስክር ወረቀት ኮፒና CPO ከኦርጅናል ደኩመንት ጋር መያያዝ አለበት አለበት

13 ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የማብራርያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ከተወሰነዉ ግዜ ገደብ በፊት በስልክ ቁጥር 0914746258 /0914722381 መጠየቅ ይችላሉ

14 ተጫራቾች በጨረታ የአፈፃፀም ሂደት ቅሬታ ካላቸዉ አቤቱታ የማቅረብ መብት አላቸዉ

15 ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ   

16 ጨረታዉ ከታሕሳስ /08 እስከ  ታሕሳስ /22 /2008 ዓ/ም ሲሆን ጨረታዉ ልክ 3:30 ተዘግቶ ልክ 4:00 ተጫራቾች ባሉበት ይከፈታል በተጨማሪም ደግሞ መንግስት ባወጣዉ አዲስ መመሪያ መሰረት 15 VAT ከአቅራቢዎች ካሸነፉበት የዕቃ ዋጋ ተቀንሶ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ የሚደረግ መሆኑና ለአሸናፊዎችም 15 VAT የተቀነሰበት ገንዘብ ስለመሆኑ ኮሌጁ ህጋዊ የገቢ ደረሰኝ የሚሰጥ መሆኑ እንገልፃለን

17 ማንኛዉም አቅራቢ ያሸነፋቸዉ ዕቃዎች ጥራት ያላቸዉ ማቅረቡን የሚታወቀዉ በኮሌጁ ናሙና ወይም ስፐስፊኬሽን መሰረት ሲሆን በትክክል ማቅረባቸዉ የሚታወቀዉ በኮሌጁ ቴክኒካል ኮሚቴ ዕቃዎቹ ገቢ ከመሆናቸዉ በፊት ታይቶ ሰረጋገጥ ብቻ ይሆናል በትክክል ጥራት የሌላቸዉ ዕቃዎች ኮሌጁ ያለመቀበል መብት አለዉ

18 ኣቅራቢዎች በዚህ ዉስን ጨረታ ሲወዳደሩ ለሚወዳደሩት ዕቃዎች ንግድ ፈቃዳቸዉ ተዛማጅነት ያለዉ መሆን አለበት

19 ተወዳዳሪ ድርጅት የሚወዳደሩበት እቃ ራሳቸዉ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ወደ ሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ በአካል ናሙና ማየት አለባቸዉ

20 ተወዳደሪዎች የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚፅፉበት ወቅት ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነና የተሰረዘ የተደለዘ ሰነድ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም

21 በቀረበዉ የኮሌጅ መሰፈርት ማሻሻያ መፃፍ አጥብቆ የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ዋጋዉ ለመሙላት አስቸጋሪ ከሆነ የሚቀርቡት አይነት መፃፍ ይችላሉ

 

 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo