የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ለኪዳነ ተክለ እና ዘርኡ አብርሃ ሕ/ሽ/ማሕበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የተያዘውን ሞዴል NPR71፣35 ኩንታል የሚጭን አይሱዙ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

ለኪዳነ ተክለ እና ዘርኡ አብርሃ ሕ/ሽ/ማሕበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የተያዘውንና በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 98/90 እና 216/92 የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው / የመያዣ ሰጪው ስም/

የሚሸጠው ንብረት ዓይነት

ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ

የጨረታው ደረጃ

የጨረታው መነሻ ዋጋ /በብር/

ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት

ኪዳነ ተክለ እና ዘርኡ ኣብርሃ ሕ/ሽ/ማሕበር

ሞዴል NPR71፣35 ኩንታል የሚጭን አይሱዙ ተሽከርካሪ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ

ሁለተኛ

590,000.00

የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ

  1. 1. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት አይነት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ፅ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን እስከ የካቲት 09 ቀን 2012 . ከቀኑ 1000 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  2. 2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ፡ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  3. 3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 10 ቀን 2012 . ከረፋዱ 400-600 በዲስትሪክቱ ፅ/ቤት ይካሄዳል።
  4. 4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸነፉት ያስያዙት ጎንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።
  5. 5. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ሲኖርበት፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
  6. 6. ገዥው ንብረቱን በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (አስራ አምስት በመቶ) መክፈል ይጠበቅበታል።
  7. 7. አሸናፊው ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት ከፈለገ የባንኩን ብድር መስፈርት ማሟላትና ቢያንስ 15% ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል
  8. 8. ስም ማዛወሪያና በሽያጩ ምክንያት የሚፈለግ ማንኛውንም የመንግስት ክፍያዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል።
  9. 9. ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር ሁኔታ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የፕሮጀክት ማስታመሚያና ማገገሚያ ቡድን በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 034441-9016 ወይም 034-441 -0233 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
  10. 10. ንብረቱን መመልከት የሚፈልግ ተጫራች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለዲስትሪክት ፅ/ቤት በግንባር ቀርቦ መመልከት ይቻላል።
  11. 11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo