የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ

  • የማር ማቀነባበሪያ ማሽን
  • የእንስሳት ህክምና መገልገያ እቃዎች
  •  አነስተኛ የእጅ እርሻ መሳሪያዎችና የመስኖ ውሃ ፍሰት መቆጣጠሪያ መሳርያ ፓርሻል ፍሉም (Parshall flume)
  • የማንጎ ፍሬ ዘር
  •  የኣይቲ እቃዎች (IT Equipments )

1 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁአቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን የተዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር /በመክፈል  መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ ከቢሮአችን የዕቃ ግዢ ንኡስ ሥራ ሂደት በስራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድየምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ፣ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፣

2 ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣የቫት ሰርቲፊኬትና ያለፈው ወር ሻት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/፣ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
3 ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው፣

4 የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በእያንዳንዱ ጨረታ ዶክመንት ላይ የተገለፀው መጠን በቢሯችን ስም በሲፒኦ አሰርተው ጨረታውከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

5 ቢሯችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 15% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፣

6 ጨረታው ሚያዝያ 15/2011ዓ/ም ከጧቱ በ3.30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4.00 ሰዓት ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች
7 ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮኣችን ዕቃ ግዢ ንኡስ ስራ ሂደት ይከፈታል፤

8 ቢሯችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፣

9 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0344-403663 ፣ 0344-404723 ወይም በፋክስ ቁጥር 0344-409971 መጠየቅ ይቻላል፡፡