ስለኛ በተሻለ እናሳውቆዎታለን.
ይህንን እንደ መልካም እድል በመውስድ ትንሽ ስለ ምልክታ.ኮም የጨረታ ማንቅያ አገልግሎት (MTAS) እንገርዎት። በማስታወቂያ ቦርዶች፣ በጋዜጣ እና በሬድዮ ሚነገሩ የጨረታ ማስታወቅያዎች ለመሰብሰብ ብዙ ችግሮች እንደሚገጥምዎትና በንግድዎ ጋሬጣ እንደሚሆንዎት በሚገባ እናውቃለን። ለእዚህ ዓላማ, እያንዳንዱን ጋዜጣ በየቀኑ ማንበብ, ሬድዮ መከታተል፣ እየተዛዛሩ በማስታወቂያ ቦርዶች ማንበብ ይኖርቦታል፣ በእርግጥ በጣም ከባድ ሥራ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። አሁን በዚህ ረገድ ያሉዎትን ችግሮች ለመፍታት የተዘጋጀን ድርጅት ነን። በትግራይ ክልልና ኣካባቢ በሚወጡት በሁሉም ዓይነት ጋዜጦች, በክልል ሬዲዮዎች እና ማስታወቂያዎች ቦርድ ላይ የታተሙ የሚወጡ የጨረታ ማስታወቅያዎች ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶችን ጨምሮ በማዘጋጅነት ልስርዎ በሚመች መንገድ በማቅረብ, ሁሉንም ዓይነት ጨረታዎችን(ግልፅ፣ ውሱን፣ፕሮፎርማ), የመንግስት እና የግል ኩባንያዎች የሚያወጡት የጨረታ ማስታወቅያዎች ለንግድ ድርጅትዎ ወይም እንደ ፍላጎትዎ አልያም ለግዢዎች ልንሰጥዎ እንችላለን. ከ 11+ አመት በላይ በዚህ አገልግሎት ውስጥ ነን, እና በቡድን ስራችን የተነሳ, ኩባንያችን በትልቅነቱ በጣም ልምድ እና አስተማማኝ ነው። በዚ ዘርፍ ተወዳዳሪና የተቆራኘ ልምድ ባላቸው ባለሙያወዎች በመታገዝ ለደንበኞቻችንን በተሻለ መንገድ ተፎካካሪ እና ብቁ እናረግዎታለን። ለዚህ ነው ለደንበኞቻችን የላቀ ጥራት ያለው ኣገልግሎት የምንሰጠው።