የጨረታ ማስታወቂያ
ለሰው ልጅ ሰው መሆን Being Human for Humanity (BHFH) የተባለ አገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የውጭ ኦዲተር (External Auditor) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፦
1. ከኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው።
2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው።
3. TOT ወይም VAT ተመዝጋቢ የሆነ።
4. ሲቪል ማህበረሰቦች ወይም ተራድኦ ድርጅቶች ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው።
5. በአካል መቐለ በሚገኘው ቢሮአችን ተገኝቶ ኦዲት ማድረግ የሚችል።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ማስታወቂያው በወጣበት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት የታሸገ የጨረታ ሰነድ በራሳቸው ወይም በወኪሎቻቸ በኩል አድርገው በመቐለ ከተማ ሞሞና ህንፃ ዘጠነኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ 09 01 75 73 10/ 09 29 06 14 19 ይደውሉ።
ለሰው ልጅ ሰው መሆን