Oromia International Bank

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ባንክ ሁመራ ቅርንጫፍ ለሰጠው ብድር በዋስትና ይዞ የነበረዉንና ተበዳሪው ዕዳቸውን በዉሉ መሠረት መክፈል ባለመቻላቸዉ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለዉ) በተሰጠዉ ሥልጣን መሠረት ባንኩ በዋስትና የያዘዉንና ለብድር ማካካሻነት የተረከበዉን የንግድ ቤት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የንብረቱም ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለዉ ቀርቧል። በመሆኑም ህንፃዉን መግዛት የሚፈልጉ ከታች በተገለፀው መስፈርት መሠረት በጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

ተ.ቁጥር

ለጨረታ የቀረበዉ ሕንፃ ኣይነት

ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት

ከተማ

ቀበሌ/ወረዳ

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት በካ.ሜ.

ቀን

ሰዓት

1

የንግድ ቤት

ሁመራ

ቀበሌ 04

ሑ/ማ/113852/ሀ-526/85

300

1,076,441.47

30-07-2017

8:30-9:30

  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን በሚገኝበት አድራሻ ቀርበዉ ማየት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሠነድ (ሲ.ፒ.ኦ) በአሮሚያ ባንክ ስም አሰርተዉና ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በፅሁፍ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዚህ በታች ባለዉ አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የመወዳደርያ ዋጋቸዉን እና የጨረታ ማስከብረያ ሲ.ፒ.ኦ. በአንድ ፖስታ ዉስጥ በማሸግ ተ.ቁ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታዉ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ. ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት በሁመራ ቅርንጫፍ ዉስጥ ይከፈታል።
  • የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በተጠቀሰዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ገቢ የማይደረግ ከሆነ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  • ጨረታዉን ያሸነፈ ተጫራች ለመወዳደሪያ ካቀረበዉ ዋጋ በተጨማሪ ለመንግሥት የሚከፍለዉን አስፈላጊ ግብርና ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ማንኛዉንም ተያያዥ ወጪዎች ይከፍላል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር በ 0342-480 030 /0918-804 946 ሁመራ ቅርንጫፍ ደዉለዉ ማነጋገር ይቻላሉ።
  • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

አድራሻ

ሁመራ ከተማ

የባንኩ ሁመራ ቅርንጫፍ በሚገኝበት ቤዛ ህንፃ ምድር ቤት

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ