አ/ኢ/ባ/ሰ/ሪ/ ጨ/ማ/ቁ/ 05/2016
ቀን 01/12/2016
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር ሰ/ሪ/ፅ/ቤት 05/2016
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ኣ.ማ ሰሜን ሪጅን ፅ/ቤት ከዚህ በፊት በዓዲ ሓውሲ በነበረው ቤት የተለያዩ ያገለገሉ የብረት በሮች እና የእንጨት በሮች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
➢ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 - 11፡00 የማይመለስ ብር 50.00 (ሓምሳ ብር) በመክፈል ከነሓሰ 01 እስከ 03 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ቀይ መስቀል አከባቢ በሰሜን ሪጅን ፅ/ቤት በመምጣት ሰነዱን በመግዛት የንብረቶቹን ዝርዝር መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
➢ በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንብረት ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ (ተ.እ.ታን ጨምሮ) 20% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ሰነድ (CPO) በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
➢ ማንኛውንም ተጫራች የሚገዛውን ንብረት አይነት በመጥቀስ የሚሰጠውን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሞልቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
➢ የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ ግልፅ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ የተደረገበት ከሆነ ማስተካከያውን በግልፅ ፅፎ በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ፈራሚ አካል ፓራፍ/ኢንሺያል ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
➢ ተጫራቾች ንብረቶቹን ከነሓሰ 01 እስከ 03 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 8.30 እስከ 10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቀዳሜ ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 2016 ዓ.ም ደግሞ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ብቻ በ ዲያስፖራ የሚገኘው መኽዝን ዕዳጋ ብዕራይ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ወይም ዲኒ ሱበር ማርኬት የሚገኝበት አከባቡ በመምጣት ማየት ይቻላል፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከሚከፍሉት ክፍያ ላይ ተቀናሽ የሚደረግላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
➢ አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ2 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ለባንኩ ከፍለው ንብረቱን በ2 ቀናት ውስጥ መረከብና ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
➢ በተባለው ጊዜ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ሲ.ፖ.ኦ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንደ አስፈላጊነቱ ሁለተኛ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች ይተላለፋል ወይም በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
➢ ንብረቱን ከማንሳት ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ወጪዎች አሸናፊ ተጫራች የሚከፍል ይሆናል፡፡
➢ አሸናፊ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡
➢ ስለእያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ቀይ መስቀል ፊት ለፊት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ሰሜን ሪጅን ፅ/ቤት በመምጣት አስፈላጊውን መረጃ መጠየቅ ይችላል፡፡
➢ ባንኩ ስለንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
➢ ይህ ጨረታ ቀን 03/12/2016 ሰዓት 10:30 ተዘግቶ ሰዓት 11:00 ተጫራች ቢገኙም ባይገኙ የሚከፈት ይሆናል።