- ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን : 1/7/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10:30
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን : ለ10 ተከታታይ ቀናት 11ኛዉ ሰኣት
ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ሠመራ በሚገኘው በዋና መ/ቤታችን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣ - ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት በደረጃ 5 የጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት የታደሰ ፈቃድ እንዲሁም የግንባታ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እና የመንግስት መ/ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አብሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ 2% ወይም ከ20ሺህ ብር ያላነሰ ዋጋ ያለው በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ) የአፋር መንገድልማት ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10:30 ሠዓት ሆኖ ወዲያውኑ ሳጥን ታሽጐ በዚያው ቀን 11ኛው ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ሠመራ ስልክ ቁጥር፡- 033 66600 79
- የመ.ሳ.ቁ 41
ፋክስ ቁጥር 033 666 0754
የአፋር መንገድ ልማት ትራንስፖርት ቢሮ