- ጨረታዉ በጋዜጣ የወጣበት ቀን - ህዳር 16/2012 : ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን - ለ15 ተከታታይ ቀናት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን - መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- ሎት-1 Audio amplifier & Corner Speaker /HomType/ with All Accessories
- ሎት-2 የህትመት ስራዎች
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ እና የታደሰ የአቅራቢዎች ሰርተፊኬት ምዝገባ ማቅረብ አለባቸው::
- ለሁሉም ሎቶች የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ቫት ዲክላሬሽን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሎት-1 የጨረታ ዋስትና ብር 30,000፣ ሎት-2 /ህትመት/ የጨረታ ዋስትና ብር 20,000 በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለሎት-1 ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ፣ ለሎት-2 ደግሞ ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ዶክሜንት በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር- 42 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች በሙሉ በሚሽጠው ጨረታ ሰነድ መመልከት ይቻላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ቫት ለሚመለከተው የሚያስገቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት ካልሆን ቫት እንዳካተተ ይቆጠራል::
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነው ከተገኙ ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለሎት- 1በ60 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ለሎት-2 ደግሞ በ45 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር-42 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው እንዲሁም 20% መጨመር አልያም መቀነስ ይችላል፡፡
- ማንኛውም ግልፅ ያልሆነ ጥያቄ ካላችሁ ጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን ከመድረሱ ከ5 ቀናት በፊት በጽሁፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት (BID VALIDITY DATE) ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
- በእያንዳንዱ ንብረት አሸናፊ ይለያል በድምር ወይም በጠቅላላ አሸናፊ አይደረግም፡፡
ለበለጠ መረጃ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
ስልክ ቁጥር 03-44-40-47-15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡