በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት፣ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማከናወን ካቀዳቸው ግዥዎች ውስጥ የእንስሳት መኖ ዘር፣ የቤለር ሣር ማሰሪያ ገመድ ፣ የዓሣ ማስገሪያ ጀልባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ሎጎ ማሰራት ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣የጽ/ መሣሪያዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና ፈርኒቸር ግዢ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Afar National Regional State Agricultural and Natural Resource Development Bureau
  • ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን  4/2/2012
    ጨረታዉ ሚዘጋበት ቀን በ15 ኛዉ የስራ ቀን በ 4:00 ሰዓት
    ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በ 15 ኛዉ የስራ ቀን በ4:30 ሰዓት
  • የእንስሳት መኖ ዘር፣
  • የቤለር ሣር ማሰሪያ ገመድ ፣
  • የዓሣ ማስገሪያ ጀልባ፣
  • አትክልትና ፍራፍሬ፣
  • ሎጎ ማሰራት ፣
  • የኤሌክትሮኒክስ፣
  • የጽ/ መሣሪያዎች እና
  • ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና
  • ፈርኒቸር ግዢ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡ 



  1. 1በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ 
  2. 1.2.የእንስሳት መድኃኒት ንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው፣ 
  3. 1.3የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው፣ 
  4. 1.4የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ 
  5. 1.5.የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TN No) ያለው፣ 
  6. 1.6ሲፒኦ ማስያዝ አለበት እና 
  7. 1.7.የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ 

2. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት፣ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ 

3. ተጫራቶች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የሕጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡ 

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና (Bid Bond) ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና እንዲሁም ናሙና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲ ያውኑ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡ 

5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡት የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም፡፡ 

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በዕለቱ 4፡30 ሰዓት በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት፣ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

7. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

8. ለተጨማሪ መረጃ በቢሮ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

 የእንስሳት፣ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ 

ሠመራ፤ 

Sponsors

The ways ideas spread.
Milkta Logo