መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በመቐለ ድህረ ሽያጭ ማእከል ፕሮጀክት የመኪና ማጠቢያ ወይም ላቫጆ (Car wash) በጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ስለሚፈልግ በኮንስትራክሽን ዘርፍ

Mesfin Industrial Engineering PLC

መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በመቐለ ድህረ ሽያጭ ማእከል ፕሮጀክት የመኪና ማጠቢያ ወይም ላቫጆ (Car wash) በጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ስለሚፈልግ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ GC-6 ወይም BC-6 እና ከዝያ በላይ ብቃት ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘዘሩትን መስፈርት የምታሞሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባነያችን ይጋብዛል::

የጨረታ መስፈርት

1 ተጫራቾች ቫት (VAT) ተመዝጋቢ እና የ2006 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆነ አለባቸዉ::

2 ተጫራቾች የማይመለስ አንድ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማያያዝ የጨረታ ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታውቅያ ከወጣበት ከ 17/08/2014 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ 25/08/2014 እ.ኤ.አ 8:00 ሰአት (ከሳት በሆላ) መቐለ ዋና መስራያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቅርንጫፍ መስራያ ቤት ለዙ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችዋል::

3 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ CPO ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በስም በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ጋር ማስገባት አለባቸው :: በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ ( CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ተቀባይነት የለዉም::

4 ጨረታዉ 25/08/2014 እ.ኤ.አ ከሳት በሆላ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ 26/08/2014 እ.ኤ.አ ከሳት በሆላ ከቀኑ 8:30 ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ መቐለ መስፍን ዋና መ/ ቤት በሚገኝ የስብስባ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸዉ የተሞላ ባይገኙም ጨረታ ሰነዱ ይከፈታል :: የስራዉ ዝርዝር ከፈለጉ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር ) በመክፈል ከመቐለ ዋናዉ ቢሮ ወይም ከአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮ መዉሰድ ይችላል::

5 ተጫራቾቸ የሚያስ ገቡት ዋጋ ቫት ( VAT) ጨምሮ መሆኑና መጠቀስ አለበት :: ይህ ካልሆነ ያስገቡት ዋጋ ቫት ((VAT) እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል ::

6 ተጫራቶች የሚያስገቡት ዋጋ ለስራዉ የሚያስፈልጉ ሁሉ (የሰዉ ሃይል " ማሽነሪና " የግንባታ ማተርያል ያጠቃለለ መሆን አለበት ::

7 ጨረታዉን አሽንፈዉ ዉል ፈፅመዉ ሳይት ከተረከቡበት ዕለት ጀምሮ በ30 ቀናት ዉስጥ ስራዉን አጠናቐዉ ማስረከብ አለባቸዉ :: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበርያ ይስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሁኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል ::

8 ተጫራቶች ለጨረታ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ሰነድ ለየብቻ አሽገዉ ማስገባት አለባቸዉ::

9 ተጫራቶች በሌላ ተጫራቶች ዋጋ ተመስርተዉ ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም ::

10 ተጫራቶች ይህን ስራ ካሸነፉ ለሌላ ሰዎስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት እይቻልም::

11 ኩባንያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ::


 

አድራሻ

አዲስ አበባ መቐለ

ስልክ +251- 116298563 ስልክ + 251- 344402017

ፋክስ +251- 116298560 ፋክስ + 251-344406225


 

Sponsors

The ways ideas spread.
Milkta Logo