የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቀሌ ቅ/ጽ/ቤት የመኪና ጎማ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል

Ethiopia Revenues and Custom Authority

የጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር ECC/MB 002/2011 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቀሌ ቅ/ጽ/ቤት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ 

  • ሎት አንድ. የመኪና ጎማ ግዥ 

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

1. ህጋዊ የታደሆይየንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡ 

2. የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ 

3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ፡፡ 

4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት 

5. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 10,000.00 ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (C.P.0) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ 

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ትራንስ ኢትዮጵያ አጠገብ የሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን መቀሌ ቅርንጫፍ የግዥና ፋይናንስ ቡድን ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በመስሪያቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 

8. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% /አስር በመቶ/ C.P.O በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡ 

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

Sponsors

The ways ideas spread.
Milkta Logo