ድርጅታችን መከላኪያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በመቐለ ከተማ ሪፈራል ሆስፒታል ለሚገነባው የመከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት ኣገልግሎት የሚውል ደብል ገቢና ፒክ ኣፕ /Double Gabin pick up/ መኪና በጨረታ ኣወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

Defence Construction Enterprise

ስለሆነም ነዳጅ ድርጅቱ ችሎ ሌላው ወጪ ባለ ንብረቱ የሚሸፍን ሲሆን በዚሁ መሰረት ለኣንድ ቀን የምታከራዩበትን ሂሳብ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት እንድታቀረቡ እያሳወቅን ተጫራቾች የሚከተሉን መስፈርቶች ማሟላት እንዳለባችሁ እናስታውቃለን፡፡

1 የታደሰ የንግድ ፍቃድ /ሊብሬ/ ማቅረብ የምትችሉ፤  

2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፤

3 በገቢዎች የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፤

4 በሊትር ምን ያህል መጓዝ እንደምትችል መግለፅ ኣለበት፤

5 የናፍታ መኪና መሆን ኣለብት፤

6 ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ፖስታ እስከ 30/06/2011ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7 ጨረታው 06/07/2011ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8 ፕሮጀክቱ የተሻላ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፤

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0914-1053/0914-730813 መደወል ይቻላል፡፡

ኣድራሻ ኣዋሽ ካምፕ ፊት ለፊት

Sponsors

The ways ideas spread.
Milkta Logo