ክፍት የጨረታ ማስታወቂያ
ፋብሪካችን ኣልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ሃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የፅሕፈት መሳሪያ እቃዎች(Stationary) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መመርያ ኣክብራችሁ ለመጫረት የምትፈጉ ተጫራቾች ሁሉ መጫረት ይምትችሉ መሆኑ በእክብሮት እንገልፃለን
የጨረታ መምርያ
1 የዚህ ጨረታ ኣላማ ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዝዉ የቀረቡ የእቃዉ ዝርዝር ማብራርያ አወዳድሮ ለመግዛት ነዉ
2 ተጫራቾች የፅሕፈት መሳሪያ እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸዉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
3 ተጫራቾች ለጨረታዉ ዉል ማስከበሪያ 50,000 በCPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ወይም በሚከፈትበት ሰዓት መስያዝ ይኖርባችዋል በጥሬ ገንዘብ የሚመጣ ተቀባየነት ኣይኖረዉም
4 ተጫራቾች ቫት ተመዝገባቢ መሆናቸዉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባችዋል
5 ተጫራቾች የሚቀረቡት ዋጋ ቫት ሳይጨምር መሆን ይኖርበታል (ነጠላ ዋጋ ከቫት በፊት ይቀምጥ)
6 ተጫራቾች ያሸነፋዋቸዉን እቃዎች በታዘዙበት ግዜ ትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ሸፍነዉ ዓድዋ በሚገኘዉ ዋና መስራቤት የማስረከብ ግዴታ ይኖርባችዋል
7 በጨረታ ዋጋ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት ኣይኖረዉም
8 የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ ቢሮ ከ 20 /11 /2007 - 20 /12/ 2007 ዓ/ም በሁሉም የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ
9 ተጫራቾች ዋጋቸዉን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በ 20 /12 /2007 ዓ/ም እሰከ ከቀኑ 4:00 ፋብሪካዉ ግቢ ፋይናንስ ቢሮ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባችዋል በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የሰነዱ ማሸግያ ፕስታ የተጫራቾች ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ መኖር ይኖርበታል
10 ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ነሓሴ 20 /2007 ዓም ከቀኑ 4:30 ሰዓት በፋብሪካዉ ዋና መስርያ ቤት ዓድዋ መሰብሰብያ ኣድራሽ ይከፈታል
11 ተጫራች ቾች በዚሁ ጨረታ ላይ ያሸነፋቸዉን እቃዎች ማሸነፋቸዉ እነደተነገራቸዉ በ5 ቀናት ዉስጥ ዉል ይፈፅማሉ ይህ ሳይሆን ሲቀር ተጫራቾች ያሰያዘዉ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል
12 ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉን ከተከፈተ በዉኃላ ጨረታዉ መሰረዝ ኣይችልም
13 ስርዝ ድልዝ የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት ኣይኖረዉም
14 ፋብሪካዉ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ በማንኛዉም ግዜ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
15 ፋብሪካዉ ለመግዛት የሚፈልጋቸዉ እቃዎች ከዚሁ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ ቀርበዋል