የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለጊዛል ጨርቃ ጨርቅ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በዋስትና የያዘውና ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና ከ47/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

The Development Bank of Ethiopia

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለጊዛል ጨርቃ ጨርቅ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በዋስትና የያዘውና ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና ከ47/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተበዳሪው መያዣ ሰጪው ሥምየመያዣ ንብረቱ አድራሻየንብረት ዝርዝርየቦታው ስፋትየሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)የሐራጁ ደረጃሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
ጊዛል ተከስታይል ኃ/የተ/ የግ ማህበርበትግራይ ብ/ክ መንግስት መቀሌ ከተማ አስተዳደር አይደር ክ/ከጅምር የህንፃ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች፣ ማሸነሪዎች፣ መሣሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች100,000 h ሜትርብር 247,858,293.09 (ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ብር ከዜሮ ዘጠኝ እንደኛ ሳንቲም)ኣንደኛግንቦት 1 ቀን 2006 ዓም ከጠዋቱ 4፡0o እስከ 7፡ዐዐ

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት

2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ከፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ብቻ አሰርተው ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ወይም ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ጨረታው ከመከፈቱ በፈት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኤ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

3. በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል።

4. ጨረታው ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ተበዳሪው ያ ሰው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። በጨረታ ቀንና ሰዓት መያዣ ሰጪው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።

5. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልፅ ደብዳቤ ከባንኩ ሲደርሰው አሸናፊ ይሆናል።

6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ5 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተገለጸው ጊዜ ውስጥ አሸናፊው ገንዘቡን ገቢ ካላደረገ ጨረታው ይሰረዛል፤ ያስያዘው ገንዘብም ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

7. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በጥሬ ለባንኩ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም አሸናፊው ንብረቱን በባንኩ ብድር ፖሊስ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ሥራ የሚያስቀጥል -ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት ማመልከት ይችላል።

መጎብኘት ይችላሉ።

8. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸውን ተሽከርካሪዎችና ማሸነሪዎችን በተመለከተ ገዢው የቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው ይገባል ወይም በንብረቶቹ ላይ በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥና ታክስ መክፈል ይኖርበታል።

9.የንብረቱ ስመ-ንብረት ለሸው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል። ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።

10. ጨረታው ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ብድሩ ከተከፈለ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠቡቀ ነው።

11. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የሽያጩን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ከፍያን ጨምሮ ይከፍላል።

12. ለተጨማሪ መረጃ በባንኩ የኦንጎዊንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ ኤንድ አኳየርድ አሴት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ ቁጥር 0 524-53-73(Extension 351) ወይም በባንኩ ዌብ ሳይት www.le.com.et. መረጃ ማግኘት ይቻላል።

Sponsors

The ways ideas spread.
Milkta Logo