- ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን : 30/12/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : በ30ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን : በ30ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
- የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ፍቃድ ያላቸው፣
- ቫት የተመዘገበና የመጨረሻ ወር ቫት ዲከለር ያደረገ ቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የጨረታው ዶክሜንት የማይመለስ 200(ሁለት መቶ) በመክፈል መቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታው ዶክሜንት ከደጋፊ ሥራ ሂደት ግዢ ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ዶክሜንቱን ማስገባት የሚቻለው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ወደ ጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች 120000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ጥሬ ገንዘብ / የተረጋገጠ ቼክ ወይም የከፍያ ትእዛዝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቹ ካሁን በፊት በጽ/ቤታችን ተወዳድሮ ያሸነፈው ንብረት 100% ካላስገባ (ካላቀረበ ) በዚህ ጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቹ ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክሜንት ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በዶክሜንቱ ከተሰጠው ስፔስፍኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ዋጋ በCPO በተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የውል ማስከበሪያ (Performance bond guarantee) 10% ማስያዝ የሚችልና በ3 ቀን ውስጥ ውል አስሮ በዶኩሜንቱ በተጠቀሰው ቀን ንብረቱን ማስገባት የሚችል፡፡
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ወደ ክልሉ ፋይናንስና ፕላን ቢሮ ደብዳቤ እንደምንፅፍ
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣውን የጨረታ ዶክሜንት ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ ለ60 ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታው እንደ አስፈላጊነቱ ከእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚቀርበውን ጨረታዶክሜንት
- 14.1 ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም
- 14.2 ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።
16. ጽ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
አድራሻ፦ ትግራይ መቐለ
መቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 0344407335 /0914755845
የመቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት
ጽ/ቤት ደ/ስ/ሂ/ፋይናንስና ግዢ አስተዳደር