በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ ጠ/መምሪያ ለ2013 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ኪራይ የሰርቪስ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defence minister Northern Command
  1.  ለሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ኪራይ 

በዚህም መሠረት ለመኪና ሰርቪስ ኪራይ በሥራው የተሰማሩ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ለሚያቀርቧቸው ሰርቪስ መኪናዎች ሙሉ ኢንሹራንስ የተገባላቸውና ስለመኪናቸው ከመንገድ ትራንስፖርት እውቅና ያገኙ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ባለንብረቶችን ይጋብዛል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ እና ዝርዝር ሰነድ የያዘ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መቐለ ኩሓ መንገድ እግሪ ወንበር አካባቢ ከሚገኘው የጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0344-41-07-50 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 

Sponsors

The ways ideas spread.
Milkta Logo