- ሎት አንድ፣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ::
- የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ወይም በትግራይ ክልል እቅድና ፋይናንስ የተዘጋጀው የአቅራቢነት ፈቃድ ማቅረብ፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ፡:
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ በተመሠከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ትራንስ ኢትዮጵያ አጠገብ ዮሐንስ ግደይ ህንፃ ከሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ ሃብት አስተዳደር ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ መጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በመስሪያ ቤቱ ሁለተኛ ፎቅ ሃብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ዋጋው ከነቫቱ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- የመኪኖቹ የስሪት ዘመን ከ2011-2019 ባለው ውስጥ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ስልክ ቁጥር፡- 0342407162/0919068385/0914830469
ፋክስ 0344407309
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን
መቐለ ቅ/ ፅ/ቤት