- የ2012 ዓ/ም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬ (TIN) የተመዘገባችሁ መሆኑን የሚገልፅ እና የባለፈው ወር የቫት (VAT) ዲክላሬሽን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችዋል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን CPO ወይ Unconditional Bank Grantee ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር ማስያዝ ይኖርባችዋል::
- ሁሉም ተጫራቶች ጨረታ ሰነድ 12/05/2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 26/05/2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍና በመቐላ በሚገኘው ዋና መስሪያቤታችን ደደቢት ብድርና ቁጠባ አ.ማ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 አስፈላጊውን ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 150/አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያሉ ቅፆችን በትክክል በመሙላት በየኣንዳንድ ገፅ በመፈረም እና ማህተም በማድረግ ምንም ገፅ ሳያጓድሉ መቐለ ዋና ቢሮ በ4ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: የጎደለ ገፅ ወይም የተዛባ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል::
- ጨረታው 26/05/2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በድርጅቱ የቀረበውን ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንዲሁም የተሟላ ዶኩሜንቱ ከሆነ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይኖሩም ከጥዋቱ 3፡30 ይከፈታል::
- የጨረታው አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ በአምስት/5/ ቀን ውስጥ ውል ማሰር ይኖርበታል::
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት እንደተገለፀ የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጠቅላላ ዋጋ 10% CPO ወይ Unconditional Bank Grantee ማስያዝ ይኖርበታል:: .
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት በ90 ቀናቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ አምጥቶ ማስረከብ የሚችል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ ዋና ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ቁጥር 11 ወይም በስልክ ቁጥር 0342-40-00-14 መቐለ ዋና ቢሮ በመደወል ማረጋገጥ የምትችሉ መሆናችሁን እንገልፃለን::
ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አክስዮን ማህበር