የኣፋር ትምህርት ቢሮ

ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን  4/2/2012

ጨረታዉ ሚዘጋበት ቀን በ15 ኛዉ ተከታታይ  የስራ ቀናት

ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በ 16 ኛዉ የስራ ቀን በ3:00 ሰዓት

ኦፊስ ፈርኒቸሮችንና ኤሌክትሮኒክሶችን በድጋሚ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1 በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ እና የግብር (ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

2 የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡመሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3 ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

4 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሳብ እና ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በመለየት በ2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣

6 ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

7 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው የስራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

9 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በስልክ ቁጥር 033-666-0125/0920 00 91 09 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት

ትምህርት ቢሮ