- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TN No. እንዲሁም የታደሰ የኣቅራቢዎች ሰርትፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
- የ 6ወር ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ
- የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ ብር 30,000 ማስያዝ የምትችሉ
- ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ዶክመት በሰም በታሸገ የተለያየ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የግዢ ንኡስ ስራ ሂደት ማስገባት አለባቸው: ኮፒ፣ ኦርጅናልና ቴክኒካል ዶከመንት የያዘው ኤንቨሎፕ ጀርባው ላይ በግልፅ መፃፍ አለበት።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ የመክፈቻው ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች በሙሉ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ መመልከት ይቻላል።
- ተወዳዳሪዎች በተሰጠው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች የሚያስገቡት ዋጋ የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ያካተተ መሆን አለበት ካልሆነ እንዳልተካተተ ይቆጠራል።
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነው ከተገኙ ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ያሸነፉትን ንብረት በ60 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ከፍለው ከመስርያቤታችን የግዥ የስራ ሂደት 4ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም 20% መጨመር አልያም መቀነስ ይችላል።
- ማንኛውም ግልፅ ያልሆነ ጥያቄ ካላችሁ ጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን ከመድረሱ ከ5 ቀናት በፊት ጥያቄያችሁን በፅሑፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት BID VALIDITY DATR) ለ60 ቀናትይሆናል።
- በእያንዳንዱ ንብረት አሸናፊ ይለያል በድምር ወይም በጠቅላላ አሸናፊ ኣይደረግም።
ለበለጠ መረጃ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ቢሮ ለመቐለ ሆስፒታል
በስ.ቁ 0932063504 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።