የመቐለ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

1. ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤት፣ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ /Dust Bin/ እና ከብረት የተሰሩ በሮችና መስኮቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ከጽ/ቤታችን ሰነድ ጨረታ በመውሰድ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ተፈላጊ መስፈርት፡-

1.ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው የንግድ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።

2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ከ30/7/2011 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከመቀሌ ከተማ ኣግአዚ ኦፕሬሽን ህንፃ በሚገኘው የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቁጥር 034 ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበት፤ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የቅርብ ወር ቫት ዲክላረሽን፣የአቅራቢነት ምዝገባ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። 

4. ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 በ CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለፋይናንሻል “አንድ” “ኦርጅናል” እና አንድ “ኮፒ” ስታሸገ ፖስታ ለየብቻቸው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን 15/08 /2011ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን በፅ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 034 ይከፈታል።

9.ተጫራቾች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር፡- 0342408757/408501 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

10. ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡