የትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ

1. በመቐለ ከተማ የመለስ አካዳሚ ሊደርሺፕ የዶርሚተሪ ብሎክ G+4 ህንፃ ግንባታ 6ተኛ ዙር በደረጃ BC-4/GC-5 እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጮች

2. በመቐለ ከተማ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማእከል ከAGP-II በተገኘ በጀት በደረጃ BC-4/GC5 እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጮች

3. በዓድዋ ከተማ የገጠር ዓድዋ አስተዳደር ህንፃ ግንባታ ለማካሄድ በደረጃ BC-5/GC-5 እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጮች

4. በሽረ እንዳስላሴ ከተማ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ህንፃ ግንባታ ከቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ፋውንዴሽን በተገፕ በጀት በደረጃ BC-5/GC-6 እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጮች

5. በሽረ እንዳስላሴ ከተማ ወተትና የወተት ተዋፅኦ ህንፃ ግንባታ ለማካሄድ ከAGP-II በተገኘ በጀት በደረጃ BC-6/GC-6 እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጮች

6. በፀለምቲ እና በወልቃይት ወረዳዎች የሃምሳ ሺ ኩንታል ስቶር ህንፃ ግንባታ ለማካሄድ ከ AGP-II በተገኘው በጀት በደረጃ BC-6/GC-6 እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጮች ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች በዚህ ጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

*የ2011 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የኮንስትራክሽን ፍቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ ያለፈው ወር የቫት ዲክላሬሽን እና የቲን ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።

*የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በህግ እውቅና ካለው ባንክ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (un Conditional bank guarantee) ወይም የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) መሰረት ከተ/ቁጥር 1 እስከ ተ/ቁጥር 4 ያሉ ፕሮጀክቶች ለእያንዳንዱ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺ ብር) ተ/ቁጥር 5 እና 6 130,000 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺ) ብር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

• ከላይ ለተዘረዘሩት የህንፃ ግንባታዎች መስፈርቶቹን ለሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ለያንዳንዱ ህንፃ ግንባታ የማይመለስ ብር በመክፈል ከተ/ቁጥር 1 እስከ ተ/ቁጥር 4 ብር 500 (አምስት መቶ) ብር ተ/ቁጥር 5 እና 6 ብር 300 (ሦስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

• ለተጨማሪ ማብራሪያ ወደ ትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የህንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 191 በአካል በመቅረብ ወይም በ 034 440 8775 የስልክ መስመር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

*ቢሮው ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

በትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን መንገድና

ትራንስፖርት ቢሮ የህንፃ

ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክተር መቐለ