ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2011
የትግራይ ክልል መንገድ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ አገልግሎት የሚውሉ
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- የፅህፈት መሳሪያ /እስቴሽነሪ/
- የማሽን /መሳሪያ/ ኪራይ /
- ኤሌክትሮኒክስ እና
- የቅየሳ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ የቲን ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መጠን በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank guarantee) ማስያዝ የሚችል፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 50.00 እና 100.00 ብር በመክፈል ከኢንተርፕራይዙ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት መውሰድ ይችላሉ፣
- የጨረታው ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ወይም በፖ.ሳ.ቁ 14 መላክ ይቻላል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተወዳዳሪ ማሸነፉ በዴብዳቤ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት በግንባር ቀርበው ውል ማሰር አለባቸው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ በዚህ ጨረታ መመሪያ የተዘረዘሩትን ለማሟላት ፍቃደኛ ካልሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው ይሰረዛል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል፣ ይሁንና 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፣
- በጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢኖሩ ይመረጣል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 0344-416727/0914734474 መጠየቅ ይቻላል።
የትግራይ ክልል መንገድ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
መቐለ