መቐለ ዩንቨርስቲ

Chereta yewetabet ken: Sep 5 2018 

መቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ

2. የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ወይም በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት በአቅራቢነት የተመዘገበ

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሚያቀርብ

5. ላለማጭበርበር በድርጅቱ ስም ቃለ መሃላ ማቅረብ የሚችል። ተ.ቁ የጨረታ አይነት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 1 የመድኃኒትና ሕክምና መገልገያ እቃዎች ግዥ ሎት-1 100,000.00 ብር 

6. ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላል።

7. ማንኛውም ተጫራች ለዚሁ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ግቢ በግ/ን/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መውሰድ ይችላል።

8. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ጊዜ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል። በ15ኛው ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ላለማጭበርበር በኮሌጁ ስም ቃለ መሃላ ማቅረብ የሚችል።