የመቐለ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

የፕሮፎርማ ማስታወቅያ(Shopping)

የመቀሌ ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅሕፈት ቤት ለመቀሌ ከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራምን ኣገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የእጅ መሳርያ(Hand tools ) እቃዎች በፕሮፎርማ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታማሉ ነጋዴዎች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል::

ተፈላጊ መስፈርቶች

1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የሻት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የቅርብ ወር ሻት ሪፖርት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ።

2. የመወዳደሪያ ሀሳቡ ከ 19/06/2017 ዓ/ም እስከ 28/06/2017 ዓ/ም ሰአት3:30 ለተጫራቾች ክፍት ሁኖ የሚቆይ ሲሆን በዚህ ቀን 3:30 ተዘግቶ 4:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 033 ይከፈታል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድንጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀሚሮ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ከመቀሌ እቅድና ፋይናንሰ ዕ/ፈት ከተማ ኣግኣዚ ኦፕሬሽን ህንፃ በመገኝዉ 1ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 033 መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና 1/ለሃንድ ቱሉስ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር ብቻ) 2/ለኤሌክትሮኒክስ ብር 15000(ኣስራ ኣምስት ሺ)በCPO ፣ በጥሬ ገንዘብ ፣ ወይም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ኣለባቸው ። የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ግዜ አንስቶ ለ15 ቀናት ይሆናል ።

5. የእቃዎች ማስረከብያ ቦታ በመስራቤታችን ግምጃ ቤት ሆኖ ማስረከብያ ግዜው ግዢው ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ይሆናል ።

6. ኣቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መፃፍ ኣለባቸው ፡፡ በቁጥር እና በፊደል በተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል ኣለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይነረዋል " በነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል።

7. ኣቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረብያ ሰንጠረዥ ውስጥ የዕቃውን ኣይነትና ብዛት ፣ ነጠላ ዋጋ ፣ እና ጠቅላላ ዋጋውን መሙላት እንዲሁም ቀን ፣ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል ።

8. ለአሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን ሙሉ ለሙሉ በውለታ መሰረት ኣጠናቅቆ ማስገባቱና ማጠናቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ ቢበዛ በ5ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ይከፈለዋል ።

9. ተጨራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን መግለፅ አለበት ። ታክስን በትክክል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ታክስ እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል ፡፡

10. አሸናፊ አቅራቢ የሚለየው ለሃንድ ቁስ ለተጠቀሱት ዕቃዎች በድምር እዕቃ ዝቅተኛ ዋጋ ኣቅራቢ (LOT based) ይሆናል ። ለኤሌክትሮኒክስ ኣይተም ቤዝ ይሆናል።

11. ግዢ ፈፃሚው መ/ቤት ከአሸናፊ ድርጅት ጋር ውለታ ከመፈራረሙ በፊት የዕቃዉን ጠቅላላ ብዛት እስከ 20% (ሃያ ፐርሰንት) ጨምሮ ወይም ቀንሶ መፈራረም ይችላል ።

12. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በፊት የዋጋ ማቅረቢያው ሰነዱን የመወዳደርያ ሀሳብ / ማስገባት ይኖርበታል ። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በኋላ የቀረበ የዋጋ ማቅረብያ ሰነድ /የመወዳደርያ ሀሳብ /ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኢንቨሎፑ ሳይከፈት ለተጫራቹ ተመላሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

0344-406747/0344-408501/0344-406839