የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ - እነ መቐለ ዩኒቨርስቲ 10 ቁ ሠዎች
በአፈ/ተከሳሽ - ተክለብርሃን አምባዬ ሃላ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር በአፈ/ተከሳሾች ተክለብርሃን አምባዬ የሚታወቁ ንብረቶች በጨረታ እንዲሸጥ ስለታዘዘ የጨረታ መነሻ ግምት ፦
1. አንድ ክሬቸር ከነ ሙሉ አክሰሰሪው ግምት ብር 7,000,000(ሰባት ሚልዮን ብር)
2. አንድ ታወር ክሬን ከነ ሙሉ አክሰሰሪው ግምቱ 3,000,000(ሦስት ሚልዮን ብር)
3. አንድ ዳምፐር ግምቱ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
4. ሁለት ስፖንዳ የሌላቸው ማርቼዲስ መኪና እያንዳንዳቸው ግምት ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር)
5. አንድ ኤሮትራከር ግምቷ ብር 1,000,000 (አንድ ሚልዮን ብር)
6. አንድ ኮንክሪት ፓምፕ 2015 ቻይና ኮድ 3-81593 ኢት ግምቷ ብር 18,000,000 (አሥራ ስምንት ሚልዮን ብር)
እነዚህ የተዘረዘሩት ንብረቶች በግልፅ ጨረታ እንዲሸጡ ስለታዘዘ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ንብረቱን በሚገኝበት በመቐለ ከተማ ዓይደር ክ/ከተማ ቀበሌ ማርያም ደሐን ቀጠና 18 ሃይለ አስገደ ፋብሪካ ሆኖ ቀን 25/06/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ረፋዱ 5፡00 ሰዓት ቀርባችሁ እንድትጫረቱ፤ የጨረታው ውጤት ደግሞ ቀን 25/6/2017 ዓ/ም 9፡00 ከሰዓት በኋላ ይቀርባል ጨረታውን ያሸነፈ ወዲያውኑ 25% ገቢ ያደርጋል የቀረውን ደግሞ በ15 ቀን ውስጥ ገቢ የሚያደርግ መሆኑን ይታወቅ ሲል የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መቐለ በተሰየመው ፍትሐብሔር ችሎት አዟል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት