የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (SWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተፃፈው እቃ በናሙና መሰረት(Sample) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል::
ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት ዝርዝር | መለኪያ | ብዛት | ማብራርያ |
---|---|---|---|---|
01 | Safty Shoes with Steel cup Industra for Welder | Pair | 297 | |
02 | Trouser & Over Coat for welder | Set | 280 | Blue Black Colour |
03 | Over all Yellow, Yellow Colour for Quality | pieces | 16 |
የጨረታ መስፈርት
1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2016 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው : የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ : የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከጨረታው ዝርዝር (ሰነድ) ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ እና ኦርጅናል የሚመለስ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከቀን ከ 05/12/2024 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ 20/12/2024 እ.ኤ.አ መቐለ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ በስራ ሰኣት መወሰድ ይኖርባቸዋል::
3. ጨረታው 20/12/2024 እ.ኤ.አ ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰኣት 8:30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል::
4 አዲስ አበባ ለሚገኙ ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰሂድ መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ መሆን አለበት::
5. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት(VAT) ጨምሮ መሆኑና አለመሆኑን በግልፅ መጠቀስ አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል::
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ ተቀባይነት የለውም::
7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት ጨምሮ 10% የውል ማስከበርያ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) በማሰራት ከኩባንያችን ጋር ውል መፈራረም አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::
8. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀናት ውስጥ እቃው ማስረከብ አለባቸው::ይህ ካልሆነ ግን ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::
9. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም::
10. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም::
11. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት እቃ መቐለ ዋና መስርያ ቤት ድረስ መጥተው ማስረከብ አለባቸው:: ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ ድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ በ10 ቀናት ውስጥ የሚፈፀም ይሆናል::
12. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ | |
---|---|
መቐለ | አዲስ-አበባ |
ስልክ-+251914702481 ፋክስ-+251-344406225 | ስልክ-+251-914726541 ፋክስ-+251-114709636 |