የኢትዮጸያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ- ቁጥር 09/2016

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግ በመተላለፍ ተይዘው የተወረሱ የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች

1. በዘርፉ የፀና ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የምችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በመሄድ ክፍያ በመፈጸም ሰነዱ ከ4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 በመሄድ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም የተጠቀሱት መረጃዎች ኮፒ በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡

3. ተጫራቾች ዕቃው ለመግዛት የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅርናጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል ፡፡

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡

የቅ/ጽ/ቤቱ ስምየንብረቱ ዓይነትጨረታው ዓይነትየንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮየጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
እስከ
መቐለ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትየንጽህና ዕቃዎችግልጽ ጨረታ22/09/201628/09/1628/09/2016 7:00 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 7፡30 ሰዓት ይከፈታል።

5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ መቐለ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው

ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

6. የጨረታ አሸናፊዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ወስጥ ተመላሽ ይደረግላችዋል፡፡

7. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸለት ጊዜ ጀምሮ 5(አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡

8. ከላይ በተ/ቁ 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

9. በጨረታ የሚሽጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጪ ባለቤት ወይም ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም::

10. ቅ/ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ መቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት +251342407107 ወይም +251342408513/ በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑ እንገልፃለን፡፡