የወረዳ ራያ ጨርጨር ገቢዎችና ፋይናንስ ጽ/ቤት

ቁጥር ወ/ራ/ጨ/ፋ-558/16

ቀን 18/08/2016 ዓ/ም

የፕሮፎርማ ማስታወቅያ

ጉዳዩ:-ለደሮ ግዥ የመወዳደሪያ ሀሳብ እንዲያቀርቡ መጠየቅ ይመለከታል፣

የወረዳ ራያ ጨርጨር ገቢዎችና ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግብርና ዕድገት ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት /AGP- II/ በተገኘ በጀት ለጨርጨር ወረዳ ገበሬዎች ድጋፍ የሚውሉ ከታች የተገለፁትን ደሮዎች መግዛት ስለሚፈልግ የመወዳደሪያ ሀሳብ እንድታቀርቡ ይጋብዛል :: መ/ቤታችን ግዥውን የሚፈፅመው በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ጫጩቶች ብቻ ሲሆን ፣ ከሚፈለጉት መጠን ለከፊሎቹ ብቻ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም ።ይህ ግዥ ተግባራዊ የሚሆነው በገንዘብና የኢኰኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በአገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላላቸው ግዥዎች አፈፃፀም ባወጣው መደበኛ የጨረታ ሠነድ ውስጥ በተጠ ቀሱት አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች መሠረት ይሆናል።አጠቃላይ የውል ሁኔታዎቹ በዚህ የመወዳደሪያ ሀሳብ መጠ የቂያ ሠነድ ውስጥ ከሌሉና ማየት ከፈለጉ መ/ቤታችንን ጠይቀው ማግኘት ይችላሉ፡፡

ክፍል " ሀ " የፍላጐት መግለጫ

1.1 የ 45 ቀን ጫጫት / ብዛት 2340 ነው ።

1.2 የማስረከቢያ ቦታ በወረዳ ራያ - ጨርጨር ስር : ባሉት ጣብያዎች ግብርናና ፅ/ቤት ባመቻቸው መሰረት በሰንጠረዡ በተዘረዘሩት ጣብያዎች ብቻ

ተ/ቁጫጩቶቹ የሚራገፉበት ጣብያየጫጩቶች ብዛትየጫቶች ቀለብ የሚራገፍበት ጣብያማብራርያ
1ወይራ ዉሃ570በጫጩቶቹ ብዛት ስታንዳርድ መሰረት 1.46 ተባዝቶ እንዲራገፍ ያደርጋል
2ባግኤ360
3ኢርባ525
4ኮርመ525
5ሓ/ኣልጋ360

የማስረከብያ ጊዘ በ 20 ቀናት ውስጥ ይሆናል ፤ይህም የግዥው ውል ከታሰረበት ቀን ጀምሮ ይሆናል

1.3 የቀረበው ዋጋ ከላይ በተራ ቁጥር 1.2 በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ሁሉ የፀና ይሆናል፡፡

1.4. ለዕቃዎቹ ዋስትና ቢያንስ የተሟላ ክትባት ለመውሳዳቸው ማረጋጋጫ ሰነድ ማቅረብ አለበት፡፡

1.5. ሰነዱ ከ18-30/08/16 ዓ/ም በወረዳ ራያ ጨርጨር ገቢዎችና ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል።

1.6.ይህ የመወዳደሪያ ሀሳብና ደጋፊ ሠነዶቹ በተመለከተው ስምምነትና ሁኔታ መሠረት መሆናቸውን በማረጋገጥና የግዥውን መለያ ቁጥር በማመልከት የሚፈፀም ይሆናል፡

1.7. የመወዳደሪያ ሀሳቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ሆኖ በ30/08/2016 ዓ.ም በ4:30 ተዘግቶ በ5፡00 በወረዳ ራያ ጨርጨር ግቢዎችና ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል።

2. የተወዳደሪዎች ዝቅተኛ ተፈላጊ መወዳደርያ ግዴታ/መሟላት ያለባቸው ዝቅተኛው መስፈርት

2.1 ተወዳዳሪዎች በዚህ ውድድር ለመሳተፍ በጨረታ መክፈቻው ቀን ከሚመለከተው የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ፅሕፈት ቤት የተሰጠ የደሮ እርባታ ስራውን በተመለከተ የብቃት ማረጋገጫ መቅረብ አለባቸው ።

2.2 ካሁን በፊት ደሮች በጥሩ ሁኔታ አሳድጎ ለተጠቃሚ ማቅረቡን ማረጋገጨ ማስረጃ ማያየዝ አለበት፡፡ ይህን ያላሟላ በግምገማ ወቅት ውድቅ ይደረጋል።

2.3 የቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ የጨረታው አሸናፊ ሊሆን የሚችለው የቴክኒክ ሁኔታዎችንና የተጠየቁት ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ከሁሉም ያነሰ ነጠላ ወይም ጠቅላላ ዋጋ ያለው ሲሆን ነው᎓᎓ ይህም በመንግሥት ግዥ አዋጅና መመሪያ መሠረት የሚፈፀም ይሆናል።

I) ተሞልቶ የተፈረመ የአቅርቦትና የዋጋ ዝርዝር፣

II) ከሚመለከተው ኣካል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ፣

III) የንግድ ፈቃዶች ፎቶ ኮፒ፣

IV) የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፤

V) በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት የተጠየቁት ሠነዶች እና መግለጫዎች፣

VI) የፕሮፎርማ ሰነድ ከወረዳ ራያ ጨርጨር ገቢዎችና ፋይናንስ ጽ/ቤት ከ18-30/08/16 ዓ/ም ከግዢ የስራ ሂደት በነፃ መዉሰድ ይቻላል

VII) የፕሮፎርማ ማስከበርያ በጥረ ገንዘብ ወይም CPO 10,000 ማስያዝ ይኖርበታል

VIII) ኣሸናፊዉ ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ የዉል ማስከበርያ ካሸነፈዉ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል

6. ያቀረብነው ዋጋ ከላይ የተጠቀሰው የመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እየገለፅን፣አሸናፊው ተጫራች በገንዘብና የኢኰኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በአገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላላቸው ግዥዎች ባወጣው ጠቅላላ : የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈጻሚ እንዲሆን የተስማማን መሆኑን እናረጋግጣለን።

7. ያቀረብናቸው የመወዳደሪያ ሀሳቦች በሰጠነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፀንተው የሚቆዩ፣የማይከለሱና ማስተካከያም የማይደረግባቸው መሆናቸውን እናረጋግጣለን።

የመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ

የአቅርቦትና የዋጋ ዝርዝር

ሆኖ

ተ.ቑየዕቃው ዓይነትመግለጫ /እስፔሲፊኬሽንመለክያብዛትየአንድ ዋጋጠቅላለ ዋጋ
1የ45 ቀንና ከዛ በላይ ዕድሜ ያላት ጫጨትና*ዝርያቸው _ቦቫይን/Bovie/
ተመሳሰይ ክብደት ፣ ቀለምና ቁመና ያላቸው
ጫጩቶቹ የ45 ቀንና ከዛ በላይ ዕድሜ የሆናቸውና ክብደታቸው 450 ግራምና ከዛ
በላይ
*45 ቀን እስኪሞላቸው ድረስ ህክምና ክትባት ያገኙ _ ከመሆናቸው በባለሙ ቁጥር ያ የተሰጠ ማረጋጋጫ ማቅረብ የሚችል
*ከመጀመርያ ጀምሮ የእንስሳት ጤና የእርባታ ባለሙያ የተሟላ ክትትል እያገኙ ለማደጋቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ መያያዝ አለበት፣
ቁጥር2340
02የተመጣጣነ ምግብየደሮዎች ቀለብ/ethio chicken/ኩ/ል34

ማሳሰቢያ

ማንኛውም ከዚህ የመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ ጋር ተያይዞ የቀረበ ተጨማሪ ሠነድ የተጫራቹ ፊርማና

ማኀተም ያስፈልገዋል፣ በመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያው የቀረቡትና ሌሎቹም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች

ፊርማና ማኅተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ይሰረዛል።

ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0914119551/0914786094 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ከሠላምታ ጋር

የወረዳ ራያ ጨርጨር ገቢዎችና ፋይናንስ ጽ/ቤት