ጨረታ ቁጥር 01/2016
የጨረታ ማስታወቂያ
የትግራይ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም፡-
- ሎት 1. ፖሊንቲቲቭ፤
- ሎት 2. አነስተኛ የእጅ የእርሻ መሳርያዎች፤
- ሎት 3. ማዳበርያ የማጓጓዝ አገልግሎት፤ በጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን፤ የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000539035658 ገቢ በማድረግ ከ15/08/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሯችን የዕቃ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
በጨረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላት ያስፈልጋል።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የ Vat ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና ያለፈው ወር ቫት (VAT) ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለባችሁ፤ ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በCPO አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ቢሯችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በ28/08/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወድያውኑ 4፡00 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሯችን የዕቃ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
- ቢሯችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች፡-034-440-3663/034-440-4346 ወይም 034-440-3663 መጠየቅ ይቻላል።
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ