የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ መለያ ቁጥር ET-TG LFSDP-399704 GO-RFB
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ሴክተር ልማት /LFSDP/ ፕሮጀክት በተገኘ በጀት ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይልፈጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን፤ የተዘጋጀው የጨረታ ዶክሜንት ብር 400 አራት መቶ/የኢትዮጵያ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000539035658 ቢሮ ሕርሻ ክልል ትግራይ በሚል ግቢ በማድረግ ከ 2/8/2016ዓ/ም ጀምሮ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሮአችን ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤ በጨረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላት ያስፈልጋል፦
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የVat ሰርተፊኬት፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) እና ሻት (Vat) ዲከለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በCPO አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቢሯችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 15% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው 2/9/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ተዘግቶ ወዲያውኑ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በቢሯችን ግዥ ክፍል ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው፤
- ቢሯችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 034 440 3663/ 034 440 4346 ወይም በፋክስ ቁጥር 034 440 9971 መጠየቅ ይቻላል።
የትግራይ ክልል ግብርና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ