የጨረታ ቁጥር ት/ክ/ኤ/አ/011/2015
የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ጐማዎች፣ ባትሪዎችና እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው።
ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነትና መጠን | ብዛት |
ሎት 1 | የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች ጐማ ከነካላማደሪያውና ፍላፕ እንዲሁም ራድያል ጐማ (7.50x16 ፣ 7.00x16 ፣ 8.25x17 ፣12.00x20 ፣ 10.00x20) | 978 |
ሎት 2 | የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች ባትሪ (12V/150A ፣ 12V/120A ፣ 12V/70A) | 88 |
ሎት 3 | የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪ ዕቃዎች /ፊልትሮዎች/ ብሬክ ፓድ እና ብሬክ ሹ | 1411 |
- በጨረታው መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑ ግብር የተፈከለበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- አድራሻ፡- መቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ ቤት 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 31፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሎት ı እና ለሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት የገንዘብ መጠን ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ በትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ምልክት በማድረግ ት/ክ/ኤ/አ/011/2015 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 31 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-34 240 6712 መደወል ይችላሉ።
የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት