የጨረታ ቁጥር: ECCMB/NCB/003/2009
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ጽ/ቤት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ፣ የደንብ ልብስ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት፣ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት ሦስት፣ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር ዕቃዎች
- ሎት አራት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ከልል ፋይናንስ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ::
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 30,000.00 ፣ ለሎት ሁለት ብር 30,000.00 ፣ ለሎት ሦስት ብር 50,000.0 እያንዳንዳቸው በባንክ በተመሠከረለት ቼክ (C.P.O) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ትራንስ ኢ/ያ አጠገብ የሚገኘውን ዮሃንስ ግደይ ህንፃ ከሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ፅ/ቤ/ት ሃብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የካቲት 11/2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመስሪያ ቤቱ አዳራሽ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10%(አስር በመቶ) C.P.O በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋው ከነቫቱ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
ስልክ ቁጥር 09 19 06 83 85/09 14 83 04 69
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ፅ/ቤት