የኢትዮጸያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታ እና መስፈርቶችን ሟሟላት የምትችሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1) ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑ/በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃደ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡ይሁን እንጂ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ግምታዊ ዋጋቸው 500,000(ከአምስት መቶ ሺ ብር) በታች ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት ማቅረብ አይገደድም፡፡ 

2) ተጫራቾች የግልፅ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ አስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ከጥዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል በፅ/ቤታችን የዕለት ገቢ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 24 በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላል፡፡

3) በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቶች እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና c.p. በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖሩበታል፡፡

4) ጨረታው ሚካሄደው በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ሲሆን በማስታወቂያው በተገለፀው ግዜ እና ቦታ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል፡፡

5) ተጫራቶች ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛ ቀን ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ናሙና ወደ መ/ቤቱ ውርስ መጋዘን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡

6) ጨረታ የሚካሄደው የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ19/03/2016 እስከ 27/03/2016 ዓ/ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ27/03/2016 ከቀኑ በ7፡30 ዓ.ም የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን በ8፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡

7) በጨረታው አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከከፈሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቶች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀው በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላችዋል፡፡

8) አሸናፊ ተጫራቶች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎች መረከብ አለባቸው፡፡

9) ከላይ በተራ ቁጥር 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታ ማሰከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለፅ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

10)ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11) ቀድሞ የእቃው ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ አካላት በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር  0910467376 ወይም በስልክ ቁጥር 0920400527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡