የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

ስማቸው ከዚህ በታች የተሰው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ተበዳሪ ከባንኩ የወሰዱትን የብድር ገንዘብ ወቅቱን ጠብቀው ተመላሽ ባለማድረጋቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 97/90 ፣98/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ አመላለስ መያዣ የሆነው ቀጥሎ የተመለከተው ፕሮጀከት ከጠቅላላ ንብረቱ ጋር በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የሐራጁ ዝርዝር መረጃ

የተበዳሪና መያዣ ለጨው ስም

ለሀራጅ የቀረበ ንብረት አይነት

የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር

የቦታው ስፋት በካ/ሜ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

ሐራጁ የሚካሄድበት  ቀን

የሐራጁ ደረጃ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

ሰዓት

ዞን

ከተማ

ቀበሌ

አቶ አታኸልቲ ሐጎስ ገ/ዝጊ

ሆቴል

7299/ድ/

2009

7037.74 ካ/ሜ

ማዕከላዊ

አክሱም

02

6/09/

2012 ዓ.ም

የመጀመሪያ

12,161,

826.80

4፡00-6፡00

ማሳሰቢያ፡

  1. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. ሐራጁ የሚካሄደው አከሱም ከተማ ቀበሌ 02 በሚገኘው በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  3. የሐራጁ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል፡፡
  6. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፣ ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት በግልፅ ያከናወናል፡፡
  7. ዝርዝር ማብራሪያ እና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት በሚገኘው፤ የኘሮጀክት ማስታመሚያና ብድር ማገገሚያ ቡድን በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ ቁጥር 0344-419016 ወይም 0344407439 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ፕሮጀክቱ በሥራ ሰዓት መጐብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከቡድኑ ጋር በመነጋገር መጐብኘት ይቻላል፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት