- ለቋሚና ለኮንትራት ሠራተኞች አልባሳት
- አላቂ የፅህፈት መሳሪያ
- ልዩልዩ የፅዳት ማቴሪያል
- ጀዲድ፤ ሻሽ እና ቁጢት
- የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ
- ለኦፊስ ማሽን ጥገና መለዋወጫ
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሕጋዊ ነጋዴ ተጫራቾች በጨረታው ሊወዳደሩ
ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ን/ፍቃድ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት የአቅራቢነት ሰርተፊኬት እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውን ያወዳድራል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዳቸው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ዓዲ-ሃገራይ የ8 ሜ/ክ/ ጦር ጠ/መምሪያ ግዥ ዴስክ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
- ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ውጪ በማጓጓዝና ለማራገፍ ዓዲሃገራይ የ8ኛ ሜ/ክ/ጦር ጠ/መምሪያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው የካቲት 13/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የክ/ጦሩ ግዥ ዴስክ በሚያዘጋጀው ቦታ ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911025079 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ
ጠቅላይ መምሪያ የ8ኛ ሜ/ክ/ጦር መ/መምሪያ