የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ET-TG LESDP-399704 GO-RFB
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ሴክተር ልማት/LFSDP/ ፕሮጀክት በተገኘው በጀት ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት ብር 300/ ሶስት መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐሌ ቅርንጫፍ በባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000539035658 ቢሮ ሕርሻ ክልል ትግራይ በሚል ግቢ በማድረግ ከ19/09/2016ዓ/ም ጀምሮ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሯችን ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ያስፈልጋል፦
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ የWat ሰርቲፊኬት፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት (Vat) ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶኩመንቱ ላይ የተጠቀሰውን መጠን ገንዘብ (በCPO አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11/10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሯችን ቢሮ ቁጥር 12 የግዥ ክፍል ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው፡፡
- ቢሯችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 034 440 3663/ 034 440 4346 ወይም በፋክስ ቁጥር 034 440 9971 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የትግራይ ክልል የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ