ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን ጥቅምት 28/2012 ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን 10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀነ 11:00 ጨረታዉ የመከፈትበት ቀን 11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00
ተቁ | የማሽን ተሽከርካሪ አይነት | ብዛት |
1 | D8H ዶዘር | 1 |
2 | ኤክስካቫተር | 1 |
3 | ሎደር ማሽን ባለ 3.5 | 1 |
4 | ግሬደር ማሽን 280 hp | 1 |
5 | ሮለር ኮምፓክተር ማሽን | 1 |
6 | ገልባጭ መኪና ባለ | 5 |
7 | የነዳጅ ቦቲ 17000 በላይ | 1 |
8 | የውሃ ቦቲ 14000 | 1 |
9 | መለስተኛ የጭነት መኪና በአይሱዙ/ | 1 |
10 | ሰርቪስ መኪና | 1 |
በዚህም መሰረት :
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሠዓት ሠመራ በሚገኘው በዋና መ/ቤታችን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርባቸው ማሽን/ ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ሊብሬ ኦርጅናሉን ይዞ በመቅረብ ጨረታውን መወዳደር ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት እና የመንግስት መ/ ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አብሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪቢያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 10,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉትjዕ ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን አፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከቀኑ 11፡00 ሠዓት ሆኖ ወዲያውኑ ሳጥኑ ታሽጐ በሚቀጥለው 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ሰመራ ስልክ ቁጥር፡-033-666-00-79
የአፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ