1 የ2011ዓ/ም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት የተመዘገባችሁ መሆኑን የሚገልፅ እና የባለፈው ወር የቫት ዲክላሬሽን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን (CPO) ወይ Unconditional Bank Guarantee 300,000.00 ብር ማዝያዝ ይኖርባችዋል፡፡
3 ሁሉም ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ 20/07/2011ዓ/ም ጀምሮ እስከ 11/08/2011ዓ/ም በኣዲስ ኣበባ ተ/ሃይማኖት ቅርንጫፍና በመቐለ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኣ/ማ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ኣስፈላጊውና ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 200.00 ብር በመክፈል ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4 ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያሉ ቅፆችን በትክክል በመሙላት በየኣንዳንድ ገፅ በመፈረም እና ማህተም በማድረግ ምንም ገፅ ሳያጓድሉ ማቅረብ ኣለባችሁ፡፡ የጎደለ ገፅ ወይም የተዛባ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
5 ተጫራቾች የተጫረቱበትን ጀነሬተሮችና ቴክኒካለና ፋይናንሻል ኣንድ ኦርጅናል ኣንድ ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ሁሉንም በትልቅ ፖስታ በማሸግ መቐለ ዋና ቢሮ በ4ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
6 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንዲሁም የተሟላ ዶክሜንቱ ከሆነ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይኖሩም 11/08/2011 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
7 የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት እንደተገለፀ በ5 ቀን ውስጥ ውል ማሰር ይኖርበታል፡፡
8 የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት እንደተገለፀ ከጠቅላላ ዋጋ 10% performance bond ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
9 ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት በ120 ቀናቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኣምጥቶ ገጥሞ ማስረከብ የሚችል፤
10 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ዋና ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ቁጥር 11 ወይም በስልክ ቁጥር 0342-40-00-14 መቐለ ዋና ቢሮ ደውለው ማረጋገጥ የምትችሉ መሆናችሁን እንገልፃለን፡፡