UNITED STEEL AND METAL INDUSTRY P.L.C

- ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው ዋና መ/ቤት በመቐለ ከተማ ሰሜን ወረዳ ወይም በኣዲስ ኣበባ ከተማ ተ/ሃይማኖት ለይላ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 የሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮኣችን ድረስ በምመጣት የንብረቶቹ ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚከተሉትን መመዘኛዎች ያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

 1 ለጨረታ ያቀሩብትን ዕቃዎች መመልከት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በፋብሪካው ቅጥር ግቢ በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡

2 የምርቶችን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በመቐለ ከተማ በወረዳ ሰሜን በሚገኘው ወይም በኣዲስ ኣበባ ከተማ ቅርንጫፍ ቢሮ ተክለሃይማኖት ለይላ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ቀርበው የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

3 ተጫራቾች የጨረታው ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖሰታ እስከ ዓርብ 27/07/2011 ዓ/ም 8፡30 ሰዓት ድረስ በፋብሪካው ዋና መ/ቤት በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ኣለባቸው፡፡

4 ጨረታው ዓርብ 27/07/2011 ልክ በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ልክ 9፡00 ሰዓት በፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በመቐለ ከተማ በወረዳ ሰሜን ላጪ የሚገኘው የመሰብሰብያ ኣዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

5 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ብር 5000.00 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6 ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በመፈፀም በራሳቸው ትራንስፖርት በኣንድ ሳምንት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው ግዜ ገደብ ካላነሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ በቅጣት መልክ ለፋብሪካው ገቢ ተደርጎ ኣሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡

7 በፖስታ ቤት ኣማካኝነት የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት ኣይኖረውም፡፡

8 ዋጋ ለመስበርና በተለያየ መንገድ ፍትሓዊ ውድድር እንዳይኖር በነጠላ ወይም በቡድን በሚንቀሳቀሱ ላይ ድርጅቱ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡

9 ድርጅታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ገዜ በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ምብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁጥር 0342-410009 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡