Ethiopia Revenues and Custom Authority

በሁመራ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ተወረሱ ንብረቶች

 ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ/17/2011

በሁመራ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገር ሲገቡና ሊወጡ ሲሉ የተያዙ የተወረሱ

  • ተሸከርካሪዎች፣
  • ሞተር ሳክሎች፣
  • ልዩ ልዩ አልባሳት፣
  • መለዋወጫዎች፣
  • ማሽኖች ፣
  • የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች እና
  • ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽና በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 በመሆኑም፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ተሽከርካሪዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በማንኛውም የንግድ ፈቃድ፤ TIN Number (የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ  ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን ያለበት ሲሆን፤ በሌሎች ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር በጨረታከሚሸጠው  ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ  ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ  ለዝግ ለጨረታ በተዘጋጀው  ሳጥን ውስጥ ማስገባት  ያለበት ሲሆን፣ ለግልጽ ጨረታው ደግሞ በጨረታው ዕለት ይዞ መምጣት ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች  የጨረታውን ሰነድ  ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡30 -6፡30 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድመቶ ብር) በመክፈል  በመቆጣጠሪያ ጣቢያው በመገኘት፣ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት  ይችላሉ፡፡
  3. በዝግ  ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው  ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ ሃያ በመቶ  (20%)  ንዲሁም ለግልፅ ጨረታ በቀረቡትተሽከርካሪዎች ላይ ለመወዳደር ለእያንዳንዱ ብር 50,000 (ሃምሣ ሺህ)  ንዲሁም በሌሎች የግልጽ ጨረታ ንብረቶች ላይ ለመወዳደር ብር50,000 (ሃምሣ ሺህ) ብቻ ለጨረታ ዋስትና (CPO) በሁመራ ጉምሩክ ከመቅረጫ ጣቢያ ስም በባንክ አሰርተው  ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
  •  

ተ.ቁ

የቅ/ፅ/ቤቱ ስም

የጨረታውአይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን ጋዜጣከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እናየመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሁመራ

ግልጽ

እስከ15/04/2011

ታህሳስ 16/2011 3፡30 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል

ዝግ

እስከ 16/04/2011

ታህሳስ 17/2011 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቹ  የሚካሄድ  ሲሆን፤ ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊትይከፈታል።
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ  ተጫራቾችደግሞ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች  ማሸነፋቸውን በደብዳቤ  ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ10  ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  4.  አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀሙ  በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  5. ከላይ በተ/ቁ 7 እና በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት  ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ  መ/ቤቱ  ገቢ ሆኖ  ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  6. ባለሥልጣኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች ፡- ሁመራ ፡- 034-848-10-33 ዋና መ/ቤት ፡- 011-667-37-95 ደውለው መጠየቅ ወይ የተቋሙን ዌብ ሳይትWWW.ERCA.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ቤተ መዛግብትና ዶክመንቴሽን ቁ 1