Government Employee Social Security Office North Region Bureau

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ሪጅን የዓዲግራት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  • ከ18 እስከ 22 ክፍል ወይም ከ200 እስከ 250 ካሬ ሜትር ሆኖ ለቢሮ አቀማመጥ እና አገልግሎት አሰጣጥ ምቹ የሆነ
  • የእያንዳንዱ ክፍል ስፋት ቢያንስ 3×4m እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • እንዲሁም ቤቱ ውሃ መብራት እና መጸዳጃ ቤት ኖሮት ከ G+3 በላይ መሆን የሌለበት ሲሆን በዓዲግራት ከተማ ይሄንን ማሟላት የሚችሉ ቤቶች መሳተፍ ይችላሉ

1.1. ከፒያሳ እስከ ዋናው መናሃርያ ግራና ቀኝ እስከ 500 ሜ ገባ ብሎ።

1.2. ከፒያሳ እስከ አጂፕ ማደያ ግራና ቀኝ እስከ 500 ሜ ገባ ብሎ።

  • ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት እና ቲኦቲ ተመዝጋቢዎች ከሆኑ የማስረጃውን ኮፒ ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚሰጡትም ዋጋ ቫት እና ቲኦቲ ያካተተ ወይንም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ያለባቸው ሲሆን ይህ ካልተገለጸ ግን የሰጡት ዋጋ ቫት እና ቲኦቲ ያካተተ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
  • ተወዳዳሪዎች ቤቱ ህጋዊ ስለመሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • እንዲሁም የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ኮፒ መቅረብ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ከሰሜን ሪጅን የዓዲግራት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቀርበው በመግዛት የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።
  • ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡- በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳያዊ ሪፐብሊክ በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ሪጅን ዓዲግራት ቅ/ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር 034 245 8636

በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

የሰሜን ሪጅን ዓዲግራት ቅ/ጽ/ቤት

NB
በኣዲስ ዘመን የወጣበት ቀና 03/08/2017 or posted on Addis Zemen Apr 11, 2025