Bureau of Culture and Tourism

የፕሮፎርማ ማስታወቂያ

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በክልሉ ደቡባዊ ዞን የሚገኘውን የቅበፃ ጊወርጊስ ገዳምን ጥገና ለማካሄድ የተለያዩ የህንፃ መሳርያዎችን ለመግዛት ስለፈለገ በዚህ ስራ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ተወዳዳሪዎች ሊያሟሉት የሚገባ

1. የ2017 ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቓድ፣ የአቅራቢነት መለያ ቁጥር /Tin number/፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቐት ማረጋገጫ እና እጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ የሚያቀርቡ።

2. በዚህ መሰረት የተዘጋጀ ዝርዝር ከቢሮአችን የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 110 ከ29/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

3. ፕሮፎርማ የሚቀርብበት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀሚሮ እስከ ቀን 02/08/2017 3፡30 ሰዓት ጠዋት ገቢ ሁኖ ይታሸጋል።

4. ፕሮፎርማ የሚከፈትበት ቀን 02/08/17 4፡00 ስዓት ቢሮ ቁጥር 109 ይሆናል፡፡

5. ይህ ፕሮፎርማ በግዥ ፈፃሚ አካልና በአቅራቢው አካል እንደ ውል ሆኖ ያገለግላል።

6. ንብረቱን በ3ቀን ውስጥ ሊያቀርብ የሚችል።

7. ቢሮአችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ተጫራቾች ሰነዳችሁን ለጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን እንድታስገቡ እናሳውቃለን።

9. አድራሻችን መቐለ ጤና ጣቢያ አካባቢ ፎቶ ደስታ ፊትለፊት የሚገኝ ኣብርሃም ደስታ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ነው፡፡

10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-14-76-94-50 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡