Ethiopian Red Cross Society Tigray Branch

ግልፅ የጨረታ ማስታወቅያ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር : የትግራይ ክልል _ ቅ/ጽ/ቤት ለሚያካሂደው PERCS/NLRC Multi Sector Tigray Crisis Emergency Response Project አገልግሎት የሚውሉ የተለያዪ የቢሮ የፐ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች -

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT/TOT) የተመዘገባችሁ

4. በአቅራቢነት የተመዘገባችሁ

5. የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 10 በስራ ሰዓት ከ03/10/2016ዓ/ም እስከ 17/10/2016 ዓ/ም መውሰድ ትችላላችሁ ::

6. ተጫራቶች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በትክክል ሞልታችሁ በማሸግ እስከ 17/10/2016 ዓ/ም ሰዓት 9፡00 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ለውድድር ለጨረታ ያቀረባቹሁት ዋጋ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ /validity period/ መጠቀስ አለበት፡፡

7. ተጫራቶች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ኣይፈቀድም፡፡

9.የጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን 17/10/2016 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ቢገኙ ይመረጣል፡፡ ሆኖም ግን ባለመገንኘታቸው : ጨረታው አይስተጓገልም፡፡

10. አሸናፊ ተጫራች ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ2 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል የማሰር ግዴታ አለበት ::

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::