- 1. የጄኔሬተር ጣራ እና የግድግዳ ልብስ እና
- 2. ስላፕ በብረት የሴራሚክ ሥራ ጨምሮ ለማሠራት ይፈልጋል
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል::
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚገኘው ትግራይ ልማት ማህበር አዲስ አበባ ቦሌ መድሃኔዓለም ህድሞና ታወር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ ብር 50 እየከፈሉ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ላይ ስም አድራሻ ስልክ ቁጥር እና ፊርማቸውና ማሕተም በግልፅ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
- ግልፅ ያልሆነ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በጽሑፍ (በስልክ) በኣካል ማቅረብ ይችላል።
- ተጫራቾች በሰንጠረዡ በተዘረዘሩትን ያንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልፅ መሙላት ይኖርባቸዋል:: ስርዝ ድልዝ ካለበት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማውን ያሳረፈ አካል መፈረም ይኖርበታል፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 (ሶስት ሺ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በድርጅቱ ስም በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኣንድ ላይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ግብር የከፈለበት የግብር ከፋይ (Tin Number) አግባብነት ያለው የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፊኬትና የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ሥራውን በስንት ቀን ጨርሰው እንደሚያስረክቡ ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር መሰረት በግልፅ ማስቀመጥ ይጠበቅባችዋል፡፡
- ድርጅቱ ቅድሚያ ክፍያ (አድቫንስ) ኣያስተናግድም ሥራውን በትእዛዙ መሰረት ሰርተው ሲያስረክቡ ጥራቱ ተረጋግጦ የሚከፈለው ይሆናል፡፡
- ጨረታው እስከ 22/6/2012 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ኣዲስ አበባ ቦሌ መድሃኒኣለም ህድሞና ታወር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-08 በታሸገ ኢንቨሎኘ ይዘው ሲቀርቡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከፅ/ቤቱ የዋጋ መስጫ ቅፅ ውጭ ዋጋውን ሞልቶ ማቅረብ ጨረታው ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ እና ሊጠቅም በሚችል መንገድ የማስኬድ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የሁሉም ሥራዎች ዲዛይን በፅ/ቤቱ ተሠርቶ ስለሚቀርብላችሁ በምታቀርቡት ዋጋ የዲዛይን ሥራ ማካተት አይኖርባችሁም::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር- 0116392670/0116393926/0985016998